በትግራይ 4.5 ሚሊየን ለሚሆኑ ዜጎች የሰብአዊ ድጋፍ መደረጉ ተገለጸ

ግንቦት 28/2013 (ዋልታ) – በትግራይ ክልል በሦስት ዙሮችና አሁንም እየተካሄደ ባለው የሰብአዊ ድጋፍ ከ4 ነጥብ 3 እስከ 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎች መደረጋቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቃል።

በዚህም መንግስት ከአጋር አካላት ጋር ባደረገው ድጋፍ 93 ወረዳዎች ተደራሽ መሆናቸው ነው የተነገረው።

16 ሚሊዮን ዶላር ግምት ያላቸው ከ79 ሺ በላይ የአደጋ ጊዜ መጠለያና ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎች ለ392ሺ 265 ተፈናቃዮች መዳረሱንም ከጽህፈት ቤቱ ያገኘነው መረጃ አስታውቋል።

አጋር አከላት ምግብ ነክ ባልሆኑ ድጋፎች ላይ ያደረጉት ተሳትፎ 33 በመቶ ብቻ በመሆኑ በክልሉ ለሚደረገው ድጋፍ ከፍተኛ ክፍተት መፍጠሩን በመረጃው ተመልክቷል።