ምክር ቤቱ የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ የተለያዩ የካቢኔ አባላት ሹመትን አፀደቀ

                     አቶ ተመስገን ጥሩነህ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ

ጥር 30/2016 (አዲስ ዋልታ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቀረበለትን የካቢኔ አባላት ሹመት በአብላጫ ድምጽ አፀደቀ።

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 15ኛ መደበኛ ስብሰባ የአስፈጻሚ አካላት ሹመት አፅድቋል።

በዚህም መሰረት፡-

  1. አቶ ተመስገን ጥሩነህ ….…………ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር
  2. አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ………የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
  3. ዶክተር መቅደስ ዳባ ……………….የጤና ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል፡፡
                                 አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ
                               ዶክተር መቅደስ ዳባ የጤና ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ