ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት አዲስ የስራ አመራር ቦርድ አባላትን ሹመት አጸደቀ

የኢዜአ የስራ አመራር ቦርድ አባላት

ታኅሣሥ 13/2015 (ዋልታ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ጉባኤ ስድስት አባላት ያሉትን የኢዜአ ስራ አመራር ቦርድ ሹመት አጸደቀ።

ምክር ቤቱ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቀረበለትን እጩዎች ዝርዝር በማየት ተወያይቶ ሹመታቸውን ማጽደቁ ተገልጿል።

በዚህም፦
1. ቢቂላ ሁሪሳ ሰብሳቢ (ዶ/ር)
2. መሀመድ ራፊ አባል
3. ሙሣ አህመድ አባል
4. ሚሊዮን ተረፈ አባል
5. ሁሪያ አሊ አባል
6. ነቢዩ ባዬ አባል

በማድረግ በአብላጫ ድምጽ የተቋሙ የቦርድ አመራሮች ሆነው ተሹመዋል።

የስራ አመራር ቦርዱ አባላትም በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ በመፈጸም ኃላፊነታቸውን መረከባቸውን የምክር ቤቱ መረጃ አመላክቷል።