ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በየካቲት 12 ሰማዕታት መታሰቢያ ቀን ላይ በመገኘት የአበባ ጉንጉን አስቀመጡ

 

84ኛው የየካቲት 12 ሰማዕታት መታሰቢያ

የካቲት 12/2013 (ዋልታ) – የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በ84ኛው የየካቲት 12 ሰማዕታት መታሰቢያ ቀን ላይ በመገኘት የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል።

በዚሁ መርሃ ግብር ላይ የአባት አርበኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን ተገኝተዋ ል።

በሰመዕታት መታሰቢያ ቀን የካቲት 12 ቀን በየአመቱ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት፤አባት አርበኞች፤ እና የህብረተሰብ ክፍሉ በስድስት ኪሎ ታስቦ ይውላል፡፡