ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድንና ሀገራዊ ለወጡን በመደገፍ በሰቆጣ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

 

የሰቆጣ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎችየድጋፍ ሰልፍ

የካቲት 12/2013(ዋልታ) – የሰቆጣ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድና በእርሳቸው አመራርነት የመጣውን ሀገራዊ ለውጥ በመደገፍ ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄዱ ነው።

የድጋፍ ሰልፉ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ በሳል አመራር በሀገሪቱ የመጣውን ለውጥ በመደገፍ እውቅና መስጠትን አላማ ያደረገ ነው።

በተጨማሪም ሰልፉ በህግ ማስከበር ዘመቻው የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የሀገር መከላከያ ሰራዊት፡ ለአማራ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ አባላት እውቅና የሚሰጥ መሆኑ ታውቋል።

በተለይም ዶክተር አቢይና መንግስታቸው ስራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ህዝቡ ከጎናቸው መሆኑን በአንድ ድምጽ የሚገለጽበት እንደሆነ ኢዜአ ዘግቧል።