ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር ሆስፒታል እና ሁለገብ ህንጻ ግንባታን አስጀመሩ

ንቦት 01/2013 (ዋልታ) – ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር ሆስፒታል እና ሁለገብ ህንጻ ግንባታን አስጀምረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መምህራን ማህበር ይሄን ሁለገብ ህንፃ ለመገንባት ማቀዱ ሊመሰገን እና ሊበረታታ ይገባል ያሉት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የከተማ አስተዳደሩም አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
ይህ የሆስፒታል እና ሁለገብ ህንጻ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ ባለ9 እና ባለ 6 መንትያ ህንጻዎች የሚኖሩት ሲሆን በሆስፒታሉ በስፔሻላይድ ደረጃ ከፍተኛ የህክምና አገልግሎት ሊሰጥ የሚችል የጤና ተቋም በውስጡ ያካተተ ነው።
የከተማ አስተዳደሩ ለመምህራን ማህበር ለሆስፒታል እና ሁለገብ ህንጻ መገንቢያ 3 ሺህ 600 ካሬ ሜትር መሬት ከሊዝ ነጻ የሰጠ ሲሆን፣ ይህም የመምህራንን መብትና ጥቅም ለማረጋገጥ ከፍተኛ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሏል።
የህንጻው ግንባታ በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን አማካኝነት የሚገነባ እንደሚሆን መገለጹን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተሪ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።