ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከዴንማርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጄፒ ኮፎድ ጋር በስልክ ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም አቶ ደመቀ በትግራይ ክልል ስለተካሄደው ሕግ የማስከበር ዘመቻ እና የሰብአዊ አገልግሎቶች ገለጻ አድርገዋል።
በአሁኑ ወቅት መንግሥት የሕግ ማስከበር ዘመቻውን አጠናቅቅ ክልሉን መልሶ መገንባት እና ማረጋጋት ላይ እየሠራ መሆኑን ለዴንማርክ የውጭ ጉዳይ ሚነኒስትር ገልጸውላቸዋል።
ጄፔ ኮፎድ በበኩላቸው ሰብዓዊ ዕርዳታ በመስጠትና የዜጎችን መብት ለማስጠበቅ የኢትዮጵያን መንግሥት በሚቻለው ሁሉ ለመደገፍ አገራቸው ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል፡፡
ሚኒስትሮቹ በተጨማሪ ስለ መጪው የኢትዮጵያ አጠቃላይ ምርጫ ላይም ተወያይተዋል፡፡