የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሶማሊያ የሚገኘው የሀገሪቱ ጦር እንዲወጣ ትዕዛዝ ሰጡ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ትራምፕ በሶማሊያ የሚገኘውን የአሜሪካ ጦር በአስቸኳይ እንዲወጣ ትእዛዝ መስጠታቸው ተሰምቷል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በሶማሊያ ያለው ጦር እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር እስከ ጥር 15 ለቆ እንዲወጣ ትእዛዝ ማስተላለፋቸውን ከፔንታጎን የወጣው መረጃ ያመላክታል፡፡

ጦሩ ላለፉት በርካታ አመታት በሀገሪቱ አልሸባብ የሚፈፅመውን የሽብር ጥቃት ሲዋጋ መቆየቱ የተጠቀሰ ሲሆን አሁን ላይ ለቆ መውጣቱ በሀገሪቱ ያለውን ብቻ ሳይሆን ቀጣናውን ስጋት ላይ የሚጥል ነው ተብሏል፡፡

ትዕዛዙ አሜሪካ በአለም አቀፍ ደረጃ እየወሰደች ያለውን ወታደራዊ ቅነሳ አካል ስለመሆኑም ነው የተነገረው፡፡

በሶማሊያ የሚገኘው አፍሪኮም የሚል ስያሜ ያለው ይህ የሰላም አስከባሪው ሃይል ቁጥሩ  ከ650 እስከ 800 እንደሚሆን አልጀዚራ በዘገባው አመላክቷል፡፡

የሪፐብሊካን ፓርቲ ተወካዩ እና ተሰናባቹ ፕሬዝደነት ዶናልድ ትራምፕ የስልጣን መንበራቸው ከማስረከባቸ በፊት የወሰኑት ውሳኔ እንደሆነ የተወሳ ሲሆን የወሰዱት ውስኔ ትክክል አይደለም በሚልም ትቸት ቀርቦባቸዋል፡፡

የወታደራዊ ሃይሉ እንደሚወጣ ቢረጋገጥም አሜሪካ ለአፍሪካውያን ያላትን አጋርነት በቀጣይነት መንግስታትን በመደገፍ ትቀጥላለች መባሉን ቢቢሲ እና አልጀዚራ ዘግበዋል፡፡