የተጎዱ ወገኖችን ለመደገፍ የሚያገለግል የህክምና ቁሳቁስ ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱ ተገለጸ

የጁንታው ቡድን የፈጸመውን የአገር ክህደት ተከትሎ የተጎዱ ወገኖችንና የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመደገፍ የሚያገለግል የህክምና አቅርቦት አዲስ አበባ መድረሱን የአለም ጤና ድርጅት የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ አስታወቀ
ድጋፉ የድንገተኛ ጊዜ የህክምና ቁሳቁስና የኮቪድ መከላከያዎችንም ያካተተ መሆኑ ተጠቁሟል።
አሁን የመጡት የህክምና ቁሳቁሶች በትግራይ ክልል ለሚሰጠው ድጋፍ እገዛ እንደሚያደርግ ኢዜአ ከአለም ጤና ድርጅት የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ መረጃ ያሳያል።