ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ሆሳዕና ገቡ

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን

ታኅሣሥ 15/2015 (ዋልታ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ዛሬ በደቡብ ክልል ሆሳዕና ከተማ ገብተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ ሆሳዕና ከተማ የገቡት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ባዘጋጀው ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከልና የመፍትሔ አቅጣጫ ለማስቀመጥ በሚመክረው መድረክ ላይ ውይይት ለማድረግ ነው ተብሏል።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ”በተጠናከረ የሕብረተሰብ ተሳትፎ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን በጋራ እንከላከል” በሚል በሆሳዕና ከተማ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር እያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

ተስፋዬ አባተ (ከሆሳዕና)