ጠ/ሚ ዐቢይ በሐዋሳ ከተማ በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት የተገነባውን የዳቦና ዱቄት ፋብሪካ መርቀው ከፈቱ

ታኅሣሥ 15/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በሐዋሳ ከተማ በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት የተገነባውን የዳቦ ፋብሪካ መርቀው ከፈቱ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት አማካኝነት ከአስራ አንድ የዳቦ ፋብሪካዎች አራተኛውን ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ማስመረቃቸውን አስታውቀዋል፡፡

በመላ ሀገሪቱ እየተገነቡ ያሉ የዳቦ ፋብሪካዎች በቀን 300 ሺሕ ዳቦ እና 42 ቶን ዱቄት የማምረት አቅም እንዳላቸው የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህም ለአካባቢው ማህበረሰቦች በተመጣጣኝ ዋጋ ያቀርባል ብለዋል።