ምዕራብ ዕዝ ጠላትን ድባቅ መምታት የሚችል የሜካናይዝድ ኃይል መገንባቱን ገለፀ


ግንቦት 16/2014 (ዋልታ)
ምዕራብ ዕዝ የጠላትን ኃይል ድባቅ መምታት የሚችል የሜካናይዝድ ኃይል መገንባቱን ገለፀ።
በምዕራብ ዕዝ የሜካናይዝድ ክፍሉ አስተባባሪ ኮለኔል ታደሰ ተበጀ እንደገለፁት የተኩስ አመራሩ እና የምድብተኛ ኃይሉ ያሳለፋቸውን የጦርነት ጊዜያት መነሻ ያደረገ በቂ ዝግጅት አድርገዋል፡፡
በሁሉም የሜካናይዝድ ኃይሎች ወታደራዊ ስልጠናዎች ተካሂደዋል ያሉት ኮለኔል ታደሰ የሜካናይዝድ ክፍሎች የሚሰጣቸውን ግዳጅ ተቀብለው የጠላትን ኃይል ድባቅ ለመምታት የላቀ የዝግጁነት ደረጃ ላይ እንደሚገኙ አብራርተዋል፡፡
ሠራዊቱ ካካሄዳቸው ውጊያዎች በርካታ ልምዶችን በመውሰድ በሁኔታዎች መሃል በየጊዜው የሜካናይዝድ ኃይሉን የማድረግ አቅም ማሳደግ መቻሉንም ገልፀዋል።
የሜካናይዝድ ክፍሎቹ ለእግረኛ ክፍለ ጦሮች የተኩስ ድጋፍ ለመስጠት እና የጠላት ኢላማዎችን በአስተማማኝ ሁኔታ ለማውደም ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁዎች ናቸው ማለታቸውን የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ያሳያል፡፡