በጤና ሚኒስትሯ የሚመራ ልዑክ በዓለም ጤና ጉባኤ ላይ እየተሳተፈ ነው

ግንቦት 16/2014 (ዋልታ) በጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የሚመራ ልዑካን ቡድን በ75 ኛው የዓለም ጤና ጉባኤ ላይ እየተሳተፈ ነው።

የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ከተከሰተ በኋላ በአካል የመጀመሪያ የሆነው ይህ የጤና ጉባኤ ግንቦት 14/2014 ዓ.ም በስዊዘርላንድ ጄኔቫ ተጀምሯል።

“ሰላም ለጤና ፤ ጤና ለሰላም” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ያለው ጉባኤ ላይ የዓለማችን የማኅበረሰብ ጤና አሁናዊና ቀጣይ ስትራቴጅክ ጉዳዮች ቀርበው ምክክርና ውይይት ይደረግባቸዋል፡፡

ጉባኤው ለአንድ ሳምንት የሚቆይ መሆኑን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡