ም/ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ ድምፃቸውን መስጠት

ም/ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ

መስከረም 20/2014 (ዋልታ) የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በደገሀቡር ከተማ ምርጫ ጣቢያ 4 በመገኘት ድምፃቸውን ሰጡ።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ በሰጡት አስተያየታቸው ይህ ምርጫ አሸናፊው አካል የህዝቡን አደራ የሚሸከምበት ጊዜ ነው ማለታቸውን የክልሉ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል፡፡