በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ

በሶማሌ ክልል 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ

መስከረም 20/2014 (ዋልታ) በጅግጅጋ ከተማ በሚገኙ የተለያዩ ቀበሌዎች ባሉ የምርጫ ጣቢያዎች የከተማው ነዋሪዎች በነቂስ በመውጣት ድምፃቸውን በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

በተመሳሳይ በደጋሀቡር ከተማ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

ህብረተሰቡ ሰላማዊና በተረጋጋ ሁኔታ ድምፅ በመስጠት ላይ መሆናቸውን ተጠቁሟል።

በምርጫ ጣቢያው አስተያየታቸውን የሰጡ የከተማው ነዋሪዎች ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሁኔታ ይጠቅመኛል፣ ያገለግለኛል ብለው ያመኑትን የህዝብ ተዋካዮች መምረጣቸውን ተናግረዋል።

ነዋሪዎቹ ከዚህ ቀደም በነበሩ ምርጫዎች ህዝቡ በነፃነትና በዴሞክራሲ መንገድ የሚፈልገውን ፓርቲና ተወካዮችን ለመምረጥ እንደማይችል ጠቁመው፣ በዘንድሮው 6ኛ ምርጫ ያለምንም ተፅእኖ በዴሞክራሲ መንገድ ድምፅ መስጠታቸውን ገልጸዋል።

የድምፅ አሰጣጡ የኮሮና ጥንቃቄ ባገናዘበ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን የገለጹት የከተማው ነዋሪዎች፣ የድምፅ አሰጣጡ በሰላም እንዲጠናቀቅ ህብረተሰቡ የሚጠበቅባቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ መጠየቃቸውን ከሶማሌ መገናኛ ብዙሃን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በደጋህቡር ከተማ ምርጫ ክልል 4 ተጀምሯል።

የደጋሀቡር ከተማ ነዋሪዎች በጠዋት ወደ ምርጫ ጣቢያው በመምጣት ድምፃቸውን በመስጠት ላይ እንደሚገኙና በደጋሀቡር ከተማ 38 የምርጫ ጣቢያዎች እንዳሉ የጀረር ዞን የምርጫ አስተባባሪ አቶ መውሊድ እስማኤል ገልፀዋል።