ሞዛምቢክ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ዘመቻ ዛሬ እንደምትጀምር ተገለጸ

የካቲት 29/2013 (ዋልታ) – ሞዛምቢክ የኮሮና ቫይረስ ክትባትን በዘመቻ መልክ ዛሬ መስጠት እንደምትጀምር ተገለጸ፡፡

በዚህም የጤና ባለሙያዎች በሥራ ወቅት ለቫይረሱ ከፍተኛ ተጋላጭ  በመሆናቸው  ክትባቱን በቅድሚያ ይወስዳሉ ተብሏል፡፡

የሞዛምቢክ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሀገሪቱ ባለፈው ወር ከቻይና ከተቀበለችው 200 ሺህ ዶዝ ውስጥ 121 ሺህ 530 ክትባቶችን ማሰራጨቱን ገልጿል፡፡

እንዲሁም ዛሬ ተጨማሪ 484 ሺህ ክትባቶችን ትቀበላለች ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ከዚህም 384 ሺህ ከኮቫክስ 100 ሺህ ደግሞ በህንድ የተሰጠ የኮቪሺልድ ክትባት እንደሚገኙበት ታውቋል፡፡

በሞዛምቢክ እስካሁን 62 ሺህ 520 ሰዎች በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሲሆን፣ 693 ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል፤ 46 ሺህ 421 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ ማገገማቸውን የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል፡፡