ርዕሰ መስተዳድሮቹ የሁለቱን ክልሎች የጋራ የሠላምና ልማት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ግንባታ አስጀመሩ

የካቲት 4/2014 (ዋልታ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሃሰን እና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የሁለቱን ክልሎች የጋራ የሠላምና የልማት ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ግንባታ በአሶሳ ከተማ አስጀመሩ።

የጽሕፈት ቤት ግንባታው በ30 ሚሊዮን ብር እንደሚከናወን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡