ሰንደቅ ዓላማችን የሁላችንም መለያ በመሆኑ ክብሩን በሁሉም ቦታ ልንጠብቅ ይገባል – የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

ፕሬዝዳንት
የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

ጥቅምት 5/2016 (አዲስ ዋልታ) ሰንደቅ ዓላማችን የሁላችንም መለያ በመሆኑ ክብሩን በሁሉም ቦታ ልንጠብቅ ይገባል ሲሉ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ።

16ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን “የሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ ለህብረብሄራዊ አንድነታችንና ሉአላዊነታችን ዋስትና ነው” በሚል መሪ ቃል በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ተከብሯል።

በዚሁ ወቅት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ እንደተናገሩት ሰንደቅ ዓላማ ከነ ልዩነታችን የሚያስተሳስረን ምልክታችን ነው።

በመሆኑም ወጣቱ ትውልድ ለሰንደቅ ዓላማው ፅኑ ፍቅር እንዲኖረው መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

በመርሀ ግብሩ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ቴዎድሮስ ምህረትና የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር አባላት ተገኝተዋል ።

የሰንደቅ አላማ ቀን በየአመቱ ጥቅምት በገባ የመጀመርያው ሰኞ ይከበራል ።

በመስከረም ቸርነት