ዋልያዎች የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ዛሬ ምሽት ያከናውናሉ

ጥር 1/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታውን ዛሬ ምሽት 4 ሰዓት ያከናውናል።
ዋልያዎቹ ከኬፕ ቨርዴ (ሰማያዊው ሻርክ) አቻቻው ጋር ነው የመጀመሪያ የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታቸውን የሚያደርጉት።
ሽመልስ በቀለ፣ ዳዋ ሁቴሳ እና ፋሲል ገብረሚካኤል በጉዳት ምክንያት ከጨዋታው ውጪ መሆናቸውም የታወቀ ሲሆን ጌታነህ ከበደም ቡድኑን በአምበልነት እየመራ ወደ ሜዳ ይገባል ተብሏል።