የማሌ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ በዓል ተከበረ

ጥር 1/2014 (ዋልታ) የማሌ ብሔረሰብ ዶኦማ የዘመን መለወጫ ክብረ በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ተከብሯል።
የማሌ ብሔረሰብ በደቡብ ኦሞ ዞን ከሚገኙ ብሔር ብሔረሰቦች መካከል አንዱ ሲሆን በየዓመቱ ጥር አንድ ወይም በብሔረሰቡ አጠራር ባሬ ፔተ አሮጌውን ዓመት ሸኝተው አዲሱን ዓመት ይቀበላሉ።
በዓሉ በብሔረሰቡ ጎሳ መሪዎች ከጥንት ጀምሮ እየተከበረ የቆየ ባህላዊ እሴት እና ሃብት ሲሆን ዶኦማ ማለት ማብሰር፣ መጀመር ወይም መቅደም የሚል ትርጓሜ እናዳለው ተገልጿል።
በክብረ በዓሉ ላይ ከፌዴራል፣ ከክልል እንዲሁም ከአጎራባች ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን የደቡብ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት ዘግቧል።