ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ሮቤ ከተማ ገቡ

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው

ግንቦት 26/2013 (ዋልታ) – ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሀዊ ጉዲና ወረዳ በጽህፈት ቤታቸው ያስገነቡትን ትምህርት ቤት ለመመረቅ ሮቤ ከተማ ገብተዋል፡፡

ወ/ሮ ዝናሽ ሮቤ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ደማቅ አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከጽ/ቤታቸው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡