በሀላባ ከ 55 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ፕሮጀክቶች እየተመረቁ ነው

ሰኔ 29/2014 (ዋልታ) በሀላባ ዞን ከ 55 ሚሊየን ብር በላይ ግንባታቸው የተጠናቀቁ የልማት ፕሮጀክቶች እየተመረቁ ነው።

የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እርስቱ ይርዳው በዞኑ ከ 55 ሚሊየን ብር በላይ የተገነቡ የጤና ተቋማት እና የአስተዳደር ህንጻ መርቀው ከፍተዋል።

ዛሬ ከሚመረቁ ፕሮጀክቶች መካከል አራቱ የጤና ተቋማት መሆናቸውን የክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

በምረቃ መርኃ ግብሩ የደቡብ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋጤ ስርሞሎ፣ የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ መሐመድ ኑርዬ (ዶ/ር) እና ሌሎች የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።