በሀረሪ ክልል የኮቪድ-19 ክትባት መሰጠት ተጀመረ

 የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ዲኤታ አለምፀሀይ ጳውሎስ

መጋቢት 4/2013 (ዋልታ) – የኮቪድ-19 ክትባት በሀረሪ ክልል በጀጎል ሆስፒታል መሰጠት ተጀምሯል።

የክትባቱን መጀመር በይፋ ያበሰሩት የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ዲኤታ አለምፀሀይ ጳውሎስ እንዳሉት በሀገሪቱ ለ2 ነጥብ 2 ሚሊየን ለሚሆን የህብረተሰብ ክፍል ይሰጣል።

በክትባት ዘመቻው ይበልጥ ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በተለይም ለጤና ባለሙያዎች ቅድሚያ ይሰጣል ተብሏል።

በአሁኑ ወቅት ክትባቱን የወሰዱ አካላት ሁለተኛ ዙር መውሰድ እንደሚገባም ሚኒስር ዴኤታዋ ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት እየታየ ያለው የመዘናጋት ችግር መቅረፍ አስፈላጊ ነው ያሉት ሚኒስትር ዲኤታዋ፣ ክትባቱን የወሰዱ አካላትም የጥንቃቄ መመሪያዎችን ተግባራዊ ማድረግ ይገባቸዋል ሲሉ ተናግረዋል።

የሀረሪ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ፈቲህ መሃዲ በክልሉ ከ7 ሺህ በላይ ክትባት እንደሚሰጥ ማስታወቃቸውን ከሀረሪ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡