በሀገራዊ ምክክሩ ዋና ዋና ጉዳዮችን በመለየት በተፈለገው ጊዜ እንዲጠናቀቅ ሁሉም ርብርብ ሊያደርግ ይገባል – አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ


ታህሳስ 16/ 2016 (አዲስ ዋልታ) በሀገራዊ ምክክሩ ትኩረት የሚሹ ዋና ዋና ጉዳዮችን በመለየት በተፈለገው ጊዜ እንዲጠናቀቅ ባለድርሻ አካላት ርብርብ ሊያደርጉ እንደሚገባ የህዝብ ተወካየች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ገለፁ፡፡

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አፈፃፀም ላይ የተደረገ የመስክ ምልከታ ሪፖርት በዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ቀርቧል።

ሪፖርቱ አፈ-ጉባዔ ታገሰን ጫፎን ጨምሮ የምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሚዲያ ተቋማት መሪዎች እና የምክክር ኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች በተገኙበት ነው የቀረበው።

አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ እንዳሉት በሀገራዊ ምክክሩ ትኩረት የሚሹ ዋና ዋና ጉዳዮችን በመለየት በተፈለገው ጊዜ እንዲጠናቀቅ ባለድርሻ አካላት ርብርብ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል።

ቋሚ ኮሚቴው በሲዳማ፣ በሀረሪና በቤንሻጉል ክልሎች እንዲሁም በኮሚሽኑ ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት የምክክር ኮሚሽኑ ተግባር እና ሂደት ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ምልከታ ማድረጉን በቀረበው ሪፖርት ተመላክቷል፡፡

በቀረበው ሪፖርት መነሻነትም ውይይት እየተደረገበት እንደሆነ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡