በሆሮ ጉድሩ ህገወጥ የጦር መሳሪያ ተያዘ

መጋቢት 22/2013 (ዋልታ) – በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በሕገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ የጦር መሣሪያ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ፖሊስ አስታወቀ።
የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የመረጃ ክፍል ባለሙያ ሳጂን ኦላና ተክሉ ለኢዜአ እንደገለጹት የጦር መሳሪያው የተያዘው በዞኑ በአሙሩ ወረዳ በአገምሣ ፍተሻ ኬላ ላይ ነው።
በወረዳውና በክልሉ ልዩ ሀይል ፖሊሶች በተደረገ ፍተሻ የጦር መሳሪያው መያዙን ተናግረዋል ።
በፍተሻው ከተያዙት የጦር መሳሪያዎች ሶስት ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች፣ 16 ቱርከ ሰራሽ ሽጉጦችና 5ሺህ 855 የክላሽ፣ የብሬልና የሽጉጥ ተተኳሽ ጥይቶች መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
በጦር መሳሪያዎቹ ዝውውር የተጠረጠሩ አራት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን አስታውቀዋል።
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛው የፌስቡክ ገፃችን
https://www.facebook.com/waltainfo
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛው የትዊተር ገፃችን
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!