ብልፅግና ፓርቲ በድሬዳዋ ከተማ የምርጫ ቅስቀሳ አካሄደ

መጋቢት 22/2013 (ዋልታ) – የድሬዳዋ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ አባላት በተለያዩ የከተማዋ አቅጣጫዎች በመዘዋወር የድጋፍ እና የቅስቀሳ ስነ-ስርዓት አካሂደዋል፡፡
በቅስቀሳው ላይ የድሬዳዋ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መብራቴ ገብረየስ ፓርቲው ለከተማዋ ዕድገት እንቅፋት የሆነውን ቻርተር ለማሻሻል በትኩረት እንደሚሰራ ቃል ገብተዋል፡፡
በተጨማሪም በከተማው ከአማርኛ ቋንቋ በተጨማሪ አፋን ኦሮሞ እና አፍ ሶማሊን (ሶማሊኛ) የስራ ቋንቋ ለማድረግ ፓርቲው እንደሚሰራ መናገራቸውን ከድሬ ዳዋ አስተዳደር መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛው የፌስቡክ ገፃችን
https://www.facebook.com/waltainfo
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛው የትዊተር ገፃችን
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!