በመዲናዋ ‘መንገድ ለሰው’ ከተሽከርካሪ ነፃ ቀን በተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ተከበረ

መጋቢት 26/2013 (ዋልታ) – በአዲስ አበባ ከተማ ‘መንገድ ለሰው’ በሚል ስያሜ በከተማ አቀፍ ደረጃ የሚካሄደው ከተሽከርካሪ ነጻ መንገዶች ቀን በከተማዋ በተመረጡ 15 አካባቢዎች ተከናውኗል፡፡

የፕሮግራሙ ዓላማም በከተማዋ ሞተር አልባ እንቅስቃሴንና አማራጭ የትራንስፖርት መንገድን በማበረታታት የትራፊክ አደጋ የማይከሰትባት ከተማን መፍጠር፣ ለኑሮ ምቹና ከብክለት የፀዳ ከባቢ አየር እንዲኖር ማድረግ እንዲሁም ጤናማ የአኗኗር ዘዴን ለማጎልበት ነው ተብሏል፡፡

በዚህም ከተሽከርካሪ ነፃ ቀን ላይ የብዙሃን የእግር ጉዞ እና የተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች፣ የብስክሌት መንዳት ልምምድ እንዲሁም ስኬቲንግ፣ ሩጫ፣ የጎዳና ላይ የአካል ብቃት እንቅስቃሴና  መሰል ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች መካሄዳቸውን ከትራፊክ አስተዳደር ኤጀንሲ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡