በመዲናዋ በቀን በአማካይ ለ2.5 ሚሊዮን ሕዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት ተሰጥቷል

ጥር 6/2014 (ዋልታ) በአዲስ አባባ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያው ስድስት ወራት በቀን በአማካይ ለ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሕዝብ አገልግሎት መሰጠቱን የትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡
በ387 የጉዞ መስመር ላይ በየቀኑ በአማካይ 3 ሚሊዮን የሚሆን ሕዝብ ከቦታ ቦታ እንዲጓጓዝ ለማድረግ ታቅዶ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ማጓጓዝ የተቻለ ሲሆን ከዕቅድ አኳያ 83 በመቶ ማሳካት መቻሉ ተገልጿል፡፡
በቀን አንበሳ የከተማ አውቶቡስ ለ510 ሺሕ 40 የትራንስፖርት ተጠቃሚዎች አገልግሎት የተሰጠ ሲሆን በሸገር የብዙኃን መደበኛ ትራንስፖርት ለ227 ሺሕ 500 ዜጎች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡
በተያያዘ በሸገር ድጋፍ ሰጪ አውቶቡስ 150 ሺሕ 150 ተጠቃሚዎችን በየቀኑ ማጓጓዝ ሲቻል በኮድ 3 ድጋፍ ሰጪ ታክሲዎች 831 ሺሕ 600 ሕዝብ እንዲጓጓዝ ተደርጓል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርተ ቢሮ መረጃ እንደሚያመላክተው በኮድ 1 ታክሲዎች፣ በሀይገር ሚድባስ፣ በአይሱዙ ቅጥቅጥ፣ በፐብሊክ ሰርቪስ አውቶቡስ በተሰጡ አገልግሎቶች ከእቅድ በላይ ማሳካት ተችሏል፡፡
ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!