የአዲስ አበባ አስተዳደር ለሶማሌ ክልል የ100 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

ጥር 6/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሶማሌ ክልል በድርቅ ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች 100 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያለው የምግብ ቁሳቁስ እና የእለት ደራሽ ድጋፍ አደረገ፡፡
ድጋፉ ለ2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ለሚሆኑ ወገኖች የሚሆን ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አማካኝነት ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፋ ሙሁመድ አስረክበዋል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ “ህመማችሁ ህመማችን ነው፤ ችግራችሁ ችግራችን ነው፤ እናንተ ላይ የደረሰው ጉዳት ሁላችንም ላይ የደረሰ ነው ይሰማናል በማለት ገልፀዋል፡፡