በሳውዲ አረቢያ ያሉ ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

ሰላም ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል

ሰኔ 10/2013 (ዋልታ) – በሳውዲ አረቢያ ያሉ ቀሪ ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ በሚቻልበት መንገድ ላይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በልዩ ሁኔታ እየተሰራ መሆኑን የሰላም ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል አስታወቁ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጨምሮ ከባለድርሻ ሚኒስትር መስሪያ ቤቶችና የፌደራል ተቋማት የተውጣጣ ኮሚቴ በሰላም ሚኒስቴር ሰብሳቢነት በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ዜጎችን የመመለስና ከቤተሰቦቻቸው ጋር የማገናኘት ተግባር ሲያከናውን መቆየቱን ሚኒስትሯ አስታውሰዋል።

አሁንም ይህንኑ ተግባር አጠናክሮ ለመቀጠል ባለድርሻ አካላት ጋር በልዩ ሁኔታ እየተሰራ መሆኑን እና ሂደቱ እንደተጠናቀቀ በሳውዲ አረቢያ ያሉ ቀሪ ዜጎች ጉዳይ በቅርቡ መፍትሄ እንደሚያገኝ ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስታውቀዋል፡፡