በምስራቅ አፍሪካ የሚታየውን የፀጥታ ችግሮች ለመከላከል የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይልን መደገፍ እንደሚገባ ተገለጸ 

የካቲት 5/2015 (ዋልታ) በምስራቅ አፍሪካ የሚታየውን የሽብር፣ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችና የፀጥታ ችግሮችን ለመከላከል የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይልን በበጀት ብሎም በሰው ኃይል መደገፍ እንደሚገባ የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማጆር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ገለጹ።

የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል 31ኛውን ስብሰባ በአዲስ አበባ እያካሔደ ሲሆን በስብሰባው ላይ የተገኙት ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ በቀጣናው ላይ የሚታየውን የሰላምና ደህንነት ችግሮችን ለመፍታት ኃይሉን በበጀትና በሰው አቅም መገንባት እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።

የጋራ ኃይሉን ለማሳደግ ያለመና በፖሊሲ ደረጃ መስተካከል ስለሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ትኩረት መደረግ እንደሚገባም ገልጸዋል።

10 አባል ሀገራት ያሉት የጋራ ግብረ ኃይሉ በኤክስፐርቶች የተሻሻለውን ፖሊሲ ከገመገመ በኋላ የጋራ ግብረ ኃይሉ ያለበትን የበጀትና የአቅም ችግር መፍታት በሚቻልባቸው ጉዳዮች እየተወያየ ይገኛል።

በዙፋን አምባቸው