በም/ጠ/ሚኒስትሩ የተመራ ልዑክ በኦሮሚያ ክልል የግብርና ስራዎችን እየጎበኘ ነው

ጥቅምት 6/2014 (ዋልታ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ ልዑክ በኦሮሚያ ክልል የግብርና ስራዎችን እየጎበኘ ነው።

በጉብኝቱ የፌዴራል እና የክልል መንግስታት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል።

የልዑኩ አባላት በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን አደአ ወረዳ ውስጥ የሚገኘው ደንካካ ቀበሌ የጤፍ ሰብል ክላስተር እየጎበኙ ሲሆን፣ ጉብኝቱ ዛሬና ነገ እንደሚቀጥል ኢዜአ ዘግቧል።

ከሰሞኑ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተመራ ልዑክ በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች የተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር የግብርና ስራዎችን መጎብኘቱ ይታወቃል።