በእንግሊዝ 43ሺህ የኮቪድ ምርመራ ውጤት ስህተት ተገኘበት

ጥቅምት 5/2014 (ዋልታ) – በቤተ ሙከራ ውስጥ በተፈጠሩ ስህተቶች ምክንያት በሀገረ እንግሊዝ ወደ 43ሺሕ ገደማ የሚሆኑ ሰዎች የኮቪድ -19 ምርመራ ውጤት በስህተት መነገሩ ተገለጸ፡፡

በኤን ኤች ኤስ እና ዱካ መረጃ አጣሪ ቡድን ምርመራ ከተደረገ በኋላ በእንግሊዝ ወልቨርሃምፕተን ቤተ ሙከራ ላይ ምርመራው ተቋርጧል።

በሀገሪቱ በደቡብ ምዕራብ ክልል ውስጥ ሌላ የኮቪድ -19 ምርመራ እንዲወስዱ እየተደረገ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ምርመራ ያደረጉ ሰዎች አዎንታዊ የጎን ንክኪ ያላቸው ቢሆንም የተነገራቸው ውጤት አሉታዊ መሆኑ ስጋቱን ማባባሱ ነው የተነገረው፡፡