በርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳው የተመራ ልዑክ የመስኖ ስንዴ ልማትን እየጎበኘ ነው

ጥር 6/2014 (ዋልታ) – በደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳው የተመራ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ልዑክ በጋሞና ወላይታ ዞኖች እየተካሄደ ያለውን የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት እየጎበኘ ነው።
አሁን ላይ ልዑኩ በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ በጋሞ ልማት ማኅበር አባያ ሐይቅ አካባቢ የለማ የስንዴ ሰብል እየተጎበኘ መሆኑን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የክልሉ መንግሥት የበጋ መስኖ ስንዴ ልማትን ለማጠናከር የተለያዩ አስፈላጊ የግብርና ግብዓቶችን እያቀረበ መሆኑንም አስታውቋል፡፡
በደቡብ ክልል በተያዘው የበጋ ወቅት በተለያዩ ዞኖች ከ11 ሺሕ ሄክታር በላይ መሬትን መስኖ በመጠቀም የቆላ ስንዴ መልማቱን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል።