በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ከግጭት አካባቢዎች እንዲርቁና ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ  ኤምባሲ አሳሰበ

ሚያዝያ 8/2015 (ዋልታ) በሱዳን ካርቱም የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ግጭት ካለባቸው አካባቢዎች እንዲርቁና ከእንቅስቃሴ እንዲቆጠቡ አሳሰበ።

ኢምባሲው በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው ማሳሰቢያ ዋና ከተማዋን ካርቱምን ጨምሮ በተለያዩ የሱዳን ግዛቶች መጠነ ሰፊ ግጭት መከሰቱን እና በነዚህ አካባቢዎች የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ጥንቃቄ እንዲደርጉ አስታውቋል።

በመሆኑም ግጭቱ ወዳለባቸው አካባቢ ባለመንቀሳቀስ፣ በግጭት አካባቢ የሚኖሩት ደግሞ ከቤት ባለመውጣት እና ሌሎች አስፈላጊ ቅድመ ጥንቃቄዎችን እንዲወስዱ መክሯል፡፡