ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለአረጋዊያን እና አቅመ ደካሞች ማዕድ አጋሩ

ሚያዝያ 8/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ለአረጋዊያን እና አቅመ ደካሞች ማዕድ አጋሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ማዕድ ያጋሩት የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።

የበዓል ማዕድ የማጋራት ሥነ ሥርዓቱ የተከናወነላቸው ከተለያዩ ክፍለ ከተሞች ለተውጣጡ 150 አረጋዊያንና አቅመ ደካሞች መሆኑም ተመላክቷል።