በሱዳን የሚገኙ የውጭ ዜጎች ሀገሪቱን ለቀው ሊወጡ ነው

ሚያዝያ 14/2015 (ዋልታ) የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች (RSF) ‘ወዳጅ’ ሲል የገለጻቸው ሀገራት ዜጎቻቸውን ከሱዳን እንዲያስወጡ ለማስቻል ሁሉንም የሱዳን አየር ማረፊያዎችን ለመክፈት መዘጋጀቱን ገለጸ።

የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የውጭ ሀገራት ዜጎችን የማስወጣት ሂደቱን እንደሚያስተባብር ማስታወቁን አልጀዚራ በዘገባው አመላክቷል።

በተያያዘ መረጃ የአሜሪካ፣ የእንግሊዝ፣ የፈረንሳይና የቻይና ዲፕሎማቶች እና ዜጎች በወታደራዊ አውሮፕላኖች ከካርቱም እንዲወጡ ሊደረግ መሆኑን የሱዳን ጦር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

የሱዳን ጦር አዛዥ አብደል ፈታህ አል ቡርሃን የውጭ አገር ዜጎቹ “በሚቀጥሉት ሰዓታት ውስጥ” የሚወጡበትን ሁኔታ ለማመቻቸት እና ለማስተባበር መስማማታቸውን መግለጫው ጠቅሷል።