በአዲስ አበባ ከተማ ከሰኞ ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ሥርዓት ብቻ እንደሚካሄድ ተገለጸ

ሚያዝያ 14/2015 (ዋልታ) በአዲስ አበባ ከተማ ከሰኞ ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ሥርዓት ብቻ እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በከተማዋ ለሚገኙ የነዳጅ ማደያ ድርጅቶች በሙሉ ባስተላለፈው ጥብቅ ትዕዛዝ ከሚያዝያ 16 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የነዳጅ ተጠቃሚ ለሆኑ አካላት በሙሉ የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ሥርዓት ብቻ እንደሚካሄድ አስታውቋል፡፡

በጥሬ ገንዘብ ክፍያ መፈጸም የተከለከለ መሆኑን ያስገነዘበው ቢሮው በዕለቱ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እንደሚያደርግም ገልጿል፡፡

በመሆኑም ከወዲሁ በቂ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ለማንኛውም የነዳጅ ተጠቃሚ አካላት የነዳጅ ሽያጭን በኤክትሮኒክስ ሥርዓት ብቻ እንዲያስተናግዱ ማሰሰቡን ከቢሮው የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡