በሲዊዲን ስቶኮልም በተካሄደው የሴቶች 1500 ሜትር ዳይመንድ ሊግ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አሸነፉ

ሰኔ 26/2015 (ዋልታ) ትላንት ምሽት በሲዊዲን ስቶኮልም በተካሄደው የ1500 ሜትር የሴቶች ዳይመንድ ሊግ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከ1ኛ እስከ 3ኛ በመውጣት አሸንፈዋል።

ፍሬወይኒ ኃይሉ ውድድሩን በ1ኛነት ያጠናቀቀች ሲሆን ድሪቤ ወልተጂ እና ሂሩት መሸሻ 2ኛ እና 3ኛ በመሆን አጠናቀዋል።

በዚሁ በስቶኮልም በተደረገው የሴቶች 5 ሺሕ ሜትር የሴቶች ውድድር ለምለም ኃይሉ እና መዲና ኢሳ 2ኛ እና 3ኛ በመሆን ማጠናቀቃቸውም ተመላክቷል።

መዲና ኢሳ የግሏን ሰዓት በማሻሻል ያጠናቀቀች ሲሆን በዚህ ውድድር 1ኛ የወጣችው ቢያትሪስ ቼቤት መሆኗን አትሌትክስ አፍሪካ መረጃ አመላክቷል።

በሌላ በኩል በ800 ሜትር የሴቶች ውድድር አትሌት ወርቅነሽ መሰለ በቀዳሚነት በመግባት ማሸነፏም ተገልጿል።