በሶሪያ የሚገኘው የአይ ኤስ መሪ በድሮን ጥቃት መገደሉን የአሜሪካ ጦር አስታወቀ

አይ ኤስ ሽብር ቡድን

ሐምሌ 6/2014 (ዋልታ) በሶሪያ የሚገኘውና ከአይ ኤስ ሽብር ቡድን ከፍተኛ አመራሮች መካከል አንዱ የሆነው ማኸር አል አጋል በአሜሪካ በተሰነዘረ የአየር ጥቃት መገደሉን የአሜሪካ ጦር አስታውቋል።

የአሜሪካ ማዕከላዊ ኮማንድ በሰጠው መግለጫ ማኸር አል አጋል በሶሪያ ሰሜናዊ ምዕራብ በደረሰ የአውሮፕላን ጥቃት መገደሉን እና የቅርብ ጓደኛው ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱን ተናግሯል።

አሜሪካ በሰሜን ምዕራብ ሶሪያ ባካሄደችው የአየር ድብደባ ነው የሽብር ቡድኑ መሪ የተገደለው፡፡

አል-አጋል ከኢራቅ እና ሶሪያ ውጭ የISIS ኔትወርክ በሌሎች አገራትም የማስፋፋት ኃላፊነት ነበረበት ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።

እንደነዚህ ያሉ የአይ ኤስ መሪዎች መወገድ አሸባሪው ድርጅት ሴራዎችን እና ዓለም አቀፍ ጥቃቶችን የመፈጸም አቅም ይቀንሳል ተብሏል።
በደረሰ አማረ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW