የሰላም አማራጭ ዐቢይ ኮሚቴ ወደ ሥራ መግባቱን አስታወቀ

ሐምሌ 6/2014 (ዋልታ) የሰላም አማራጭ ዐቢይ ኮሚቴ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ወደ ሥራ መግባቱን አስታውቋል።

የኮሚቴው አባል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የሰላም አማራጭ ዐቢይ ኮሚቴው የመጀመሪያ ስብሰባ ማካሄዱን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል።

አምባሳደር ሬድዋን እንዳሉት ኮሚቴው በአፍሪካ ሕብረት መሪነት ለሚካሄደው ንግግር የራሱን የአሰራርና ሥነ ምግባር አካሄድ ተወያይቶ ወስኗል።

በንዑሳን ኮሚቴዎች በመደራጀት ኃላፊነት ተከፋፍሎ ሥራውን እንደጀመረም አስታውቀዋል።

በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ያለውን ችግር ለመፍታት መንግሥት ሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በሰብሳቢነት የሚመሩት በአጠቃላይ ሰባት አባላት ያሉት የሰላም አማራጭ ዐቢይ ኮሚቴ መሰየሙ ይታወሳል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW