በቀጣዩ ምርጫ ሰብአዊ መብት የፖለቲካ ፖርቲዎች ዋነኛ አጀንዳ ሊሆን ይገባል – የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን

 

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር

የካቲት 11/2013 (ዋልታ) – የ2013 አገራዊ ምርጫ ሰብዓዊ መብቶችን ባከበረ መልኩ እንዲከናወን የሚያስችል የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንና የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ህብረት በጋራ ያዘጋጁት “ምርጫና ሰብዓዊ መብት ” በሚል ባለድርሻ አካላት የታደሙበት የውይይት መድረክ እየተደረገ ነው።

እንደ ኢዜአ ዘገባ የኢ.ሰ.መ.ኮ ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ ሰብዓዊ መብት ድርጅቶች በ2013 የአትዮጵያ ምርጫ ሶስት ጉዳዮችን ታሳቢ ባደረገ መንገድ እንዲደረግ ይሰራል ነው ያሉት።

በዚህም በምርጫ የመሳተፍ የዜጎች መብት ማስጠበቅ፣ በምርጫ ወቅት ልዩ ትኩረት የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች ማለትም ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞችና የአገር ውስጥ ተፈናቃዮችን በምርጫ የሚኖራቸው የፖለቲከ ተሳትፎ ማስጠበቅ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ጉዳይ የምርጫው አጀንዳ በማድረግ ተወዳዳሪ ፖለቲከኞችን ቃል ማስገባትና ቢመረጡ ገቢራዊ እንዲያደርጉ ማስቻል ይገባል ነው የተባለው።

የኢ.ሰ.መ.ድ.ህብረት ፕሬዝዳንት አቶ መሱድ ገበየሁ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች በምርጫ ታዛቢነትና በሌሎች ተሳታፊ የሚሆኑበትና ምርጫው ሰብዓዊ መብቶችን ባከበረ መንገድ እንዲከናወን የሚያስችል እንዲሆን በጋራ ይሰራሉ ብለዋል ።