በቤልጂየም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ221 ሺሕ ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ

ታኅሣሥ 12/2014 (ዋልታ) በቤልጂየም አንቶርፐን ከተማ የሚኖሩ የኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ221 ሺሕ ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ፡፡

በቤልጂየም አንቶርፐን ከተማ የሚኖሩ የኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራ ማኅበረሰብ አባላት በጦርነቱ የተጎዱ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም እየተደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ የኮሚኒቲው ተወካይ በሆኑት አብነት አክሊሉ አማካኝነት ከ221 ሺሕ ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል።

ገንዘቡን የተቀበሉት በብራስልስ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሂሩት ዘመነ በአንቶርፐን የሚገኘውን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አመስግነው በዚህ ከባደ ወቅት ለተደረገው አስተዋጽኦ ማመስገናቸውን በብራሰልስ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

 
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
https://www.facebook.com/waltainfo
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
https://bit.ly/3vmjIZR
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/WALTATVEth
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!