በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የተመራ የክልል ርዕሳነ መስተዳደሮች ልዑክ ወደ መቀሌ ገቡ

ሚያዚያ 19/2015 (ዋልታ) በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የተመራ የክልል ርዕሳነ መስተዳደሮች ልዑክ ወደ መቀሌ ገብተዋል።

የሁሉም ክልል ርዕሰ መስተዳደሮቹ እና የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች በመቀሌ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የመቀሌ ከተማ ነዎሪዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የርዕሳነ መስተዳደሮቹ የመቀሌ ጉዞ ለትግራይ ክልል አጋርነታቸውን ለማሳየት እና በመልሶ ግንባታ ሂደት የድርሻውን ለማበርከት ዓላማ ያደረገ ነው።

የክልል ርዕሳነ መስተዳደሮች፣ የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባዎች ወደ መቀሌ ሲያቀኑ ከሰላም ስምምነቱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ሲል የዘገበው ኢቢሲ ነው።

ከሰሞኑ በወዳጅነት አደባባይ በተካሄደው ‘ጦርነት ይብቃ፤ ሰላምን እናፅና’ በሚል መሪ ቃል በተካሄደ መርሐ ግብር ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች በመቀሌ ጉብኝት እንደሚያደርጉ መናገራቸው ይታወሳል።