በተባበረ መንፈስ በመስራት ልማታችንን ልናረጋግጥ ይገባል – ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

ሰኔ 02/2013 (ዋልታ) – በተባበረ መንፈስ በመስራት ልማታችንን ልናረጋግጥ ይገባል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡

የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር (ጉልባማ) ከተማ አቀፍ የምክክር መድረክ እያካሄደ ሲሆን፣ በመድረኩ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ከአባቶቻቹ እንደተማራቹ አንድነታችሁን አጠናክራችሁ ቀጥሉ” የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።

የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር (ጉልባማ) ከመንግስት ጎን በመቆም የተጀመረውን ሁለንተናዊ ለውጥ ለማስቀጠል እንደሚሰራም በመድረኩ አስታውቋል።

ጠንካራ አንድነት በህብረተሰብ መካከል ተፈጥሮ ዘላቂ ልማት እንዲሰፍን እንደሚሰራ ያስታወቀው የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር፣ ከመንግስት ጎን በመቆም አስፈላጊውን ትብብር እንደሚያደርግም ጠቁሟል።

በመድረኩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ርዕቱ ይርዳው እንዲሁም ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

(በሱራፌል መንግስቴ)