በትግራይ የንጹሃን ዜጎች ሞትን በተመለከተ የሚወጡ መረጃዎች የተሳሳቱና ያልተረጋገጡ መሆናቸው ተገለጸ

በትግራይ የሰላማዊ ንጹሃን ዜጎች ሞትን በተመለከተ የሚወጡ መረጃዎች የተሳሳቱና ያልተረጋገጡ መሆናቸው የመረጃ ማጣሪያው አስታወቀ፡፡

መረጃ ማጣሪያው ባወጣው መግለጫ ህግን በማስከበር እምርጃው ወቅት የተከሰተ ማንኛውም ሞት መንግስት እንደሚያሳዝነው ገልጿል።

የአንድ ግለሰብ ሞትም በጣም ብዙ ነው በማለት አስፍሯል።

ሆኖም በነበረው ህግን የማስከበር እርምጃ በመከላከያ ሰራዊት ጥንቃቄ የተሞላበት እቅድ እና ሙያዊ ስነ ምግባር በሰላማዊ ዜጎች ላይ ጉልህ ጉዳት ማጋጠሙን የሚያሳይ መረጃ እንደሌለ ነው የገለፀው።