በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የተካሄዱ ሰልፎች ውጤታማ እንደነበሩ ተገለጸ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ለመደገፍ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የተካሄዱ ሰልፎች ውጤታማ እንደነበሩ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ገለጸ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ለመደገፍ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የተካሄዱ ሰልፎች ውጤታማ እንደነበሩ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ገለጸ፡፡

ሠልፈኞቹ የተወሰደውን የሕግ ማስከበርና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያስመዘገቡትን ውጤት የሚኮንኑ እንዲሁም የሚያጣጥሉ ኃይሎችን መቃወማቸውን ያስታወቁት አቶ ጌታቸው፣ እነዚህ ኃይሎች ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰሩትን ስራ ማጣጣል የለባቸውም፣ እነዚህን ኃይሎችን እንቃወማለን፣ ጽንፈኞች ናቸው፣ አገር የሚበትኑ ናቸው” የሚሉ መፈክሮችን ይዘው አደባባይ መውጣታቸውን ገልጸዋል።

ህብረተሰቡ “ጠቅላይ ሚኒስትሩን ሙሉ ለሙሉ እንደግፋለን፣ ፓርቲያቸውን እንደግፋለን፣ መደገፋችንንም በሰላማዊ ሰልፍ መግለጽ አለብን” በማለት ጠይቀው ሰልፍ መውጣታቸውን ያመለከቱት አቶ ጌታቸው፣ በጥያቄው መሰረትም መንግስት ጸጥታ የማስከበር ስራ መስራቱን አስታውቀዋል፡