በቶክዮ ማራቶን ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ድል ቀናቸው

የካቲት 26/2015 (ዋልታ) በ2023 በቶክዮ ማራቶን የተሳተፉ ኢትዮጵያዊን አትሌቶች በሁለቱም ጾታዎች ድል ቀንቷቸዋል።
በወንዶች ማራቶን የተሳተፈው አትሌት ደሶ ገልሚሲ በአንደኝት ሲያጠናቅቅ፤ አትሌት መሀመድ ኢሳ በሁለተኛነት፣ አትሌት ጸጋዬ ከበደ ደግሞ ሶስተኛ በመውጣት ውድደሩን በበላይነት አሸንፈዋል።
አትሌቶች ፀሓይ ገመቹ፣ አሸቴ በከሬ፣ እና ወርቅነሽ ኢዶሳ በቅደም ተከተል ከሁለተኛ እስከ አራተኛ ደራጃን ይዘው በሴቶች መራቶን በመሳተፍ አጠናቀዋል።