ጠ/ሚ ዐቢይ ከሼክ ተሚም ኢብን ሀማድ አልታኒ ጋር ተወያዩ

የካቲት 26/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሼክ ተሚም ኢብን ሀማድ አልታኒ ጋር ተወያዩ፡፡

ውይይቱ የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን ጨምሮ በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ዘርፎች ለኳታር ኢንቨስትመንቶች ብዙ ዕድሎች ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኳታር በነበራቸው ቆይታ የኳታርን ግዛት አሚር አባት ሼክ ሃማድ ቢን ካሊፋ አል ታኒንም አነጋግረዋል።

ውይይታቸውም በኢትዮጵያ ውስጥ ማኅበራዊ ልማትን እና ኢንቨስትመንቶችን በመደገፍ ላይ ያተኮረ ነበር።

እንዲሁም ከሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ጄኔራል አብደል ፈታሕ አል ቡርሃን እና ከየመን ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕን አብዱልማሊክ ሰኢድ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ መምከራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡