በቻይና ሻንጋይ በተካሄደው ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸነፉ

ሚያዝያ 19/2016 (አዲስ ዋልታ) በቻይና ሻንጋይ በተካሄደ የዳይመንድ ሊግ ውድድር አትሌት ሰሎሞን ባረጋ በ5 ሺሕ ሜትር ውድድር አሸናፊ ሆኗል።

አትሌቱ ርቀቱን ለማጠናቀቅ 12 ደቂቃ ከ55 ሰኮንድ ከ68 ማይክሮ ሰኮንድ መውሰዱን የዓለም አቲሌትክስ መረጃ አመላክቷል፡፡

በሌላ በኩል በሴቶች የ5 ሺሕ ሜትር የቻይና ሻንጋይ ዳይመንድ ሊግ 2024 ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከአንደኛ እስከ አራተኛ ደረጃ በመውጣት ውድድሩን በበላይነት አጠናቅቀዋል፡፡

በዚህም ውድድሩን በአንደኝነት ያጠናቀቀችው አትሌት መቅደስ ዓለምሸት ርቀቱን በ14 ደቂቃ ከ36 ሰኮንድ በሆነ ጊዜ በመግባት አሸንፋለች፡፡

ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት አያል ዳኛቸው በ16 ማይክሮ ሰከንድ ብቻ ተቀድማ ሁለተኛ ደረጃን ስትይዝ ለተሰንበት ግደይ ሦስተኛ ደረጃ እንዲሁም ውብርስት አስቻለ አራተኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቃቸውን የዋች አቲሌትክስ መረጃ ያመላክታል፡፡